Tuesday, April 12, 2011

ተመስገን ! ጌታ ሆይ

ተመስገን ! ጌታ ሆይ

አንተ ያረክልን
መች ከሆድ ይጠፋል
ሞትን ለኛ ሞተህ

እኛን አትርፈሃል ::
ሞትን ለኛ ሞቶ
ለሚያኖረን ጌታ
ምስጋና ይገባዋል
ሁሌ ጠዋት ማታ።
አ እዋፋት ዘምረው
እንሰሳትም ጮ

ሰማይና ምድርም

እንዲሁ ተማክረው
ያመሰግኑሃል
ልባቸውን ከፍተው
::
ይብላኝ ለከሃዲው
ለዚያ ለይሁዳ አምላኬ በስምህ
በክህደት ተጎዳ ::
አረ አንተስ ልዩ ነህ

ፍቅርህ መቼ ያልቃል
ጥሎህም የሄደው
በፍቅርህ ይወድቃል ።
ተመስገን ጌታዬ
ሁሌ ጠዋት ማታ
አንተ ያለም ንጉስ
የሁሉ አለኝታ ።
                                                                       ዳግም
- ፍቅሩ
                                                                         4/12/2011

የመቃብር ላይ ጥቅሶች

የመቃብር ላይ ጥቅሶች ...

by Dagem-Fikru on Tuesday, April 12, 2011 at 9:56am

"ስም ከመቃብር በላይ ይውላል" ፡፡ በሚለው ተለምዶአዊ አባባል መነሻነት ጽሁፌን እቀጥላለሁ ። ሰው አካባቢውን ፤ ቤተሰቡን ፤ አስተዳደጉን መስሎ እንደሚያድግ ሀቅ ነው ። ይህ ተፈጥሮአዊ የሰው ልጅ ባህሪ ነጸብራቅ ነው ። ከዚያም ባሻገር ደግሞ በስራው ዘርፍ የሚያደርገው አስተዋጽኦ እንደየሁኔታውና እንደባለቤቱ ጥረት ፡ግንዛቤ እና ምቾት ይወሰናል ። ስለሆነም ሰው በህይወት ዘመኑ ሲኖር በተለያዩ የህይወት ውጣ ውረድ መንገዶች ውስጥ ያልፋል ። ይህም..
በመልካም አልያም ከዚያ በተቃራኒው መልኩ ማለት ነው። በዚህም የምድር ኑሮ የሆነለት ሰርቶ ንብረት አፍርቶ ወልዶ ከብዶ አንቱ ተብሎ ከህይወቱ በሞት ሲሰናበት። ሌላኛው ደግሞ በህይወቱ ሳይደሰት እንደለፋ እንዳዘነ የህይወት ጣእሙ ሳይገባው እሱም ያልፋል ። ይሁን እንጂ የምድር ህይወት ደላም ቆረቆረም የመጨረሻው መደምደሚያና መብቂያ የሚሆነው ሞት መሆኑ የማያጠያይቅ ሀቅ ነው ። እንግዲህ እዚህ ላይ ነው .....ስም ከመቃብር በላይ ወይስ....? የሚለውን አባባል ። እኔም ለፅሁፌ መግቢያ ያደረኩት ። ስለዚህም ከላይ በጥቂቱ ለመግለጽ የሞከርኩት ሀሳብ እንዳለ ሆኖ ....
ወደ ዋናው ጽሁፍ ስመለስ ..ለማንሳት የፈለኩት በመቃብር ላይ የሚጻፉትን አንዳንድ አባባሎች ወይም ጥቅሶች ምን ይላሉ የሚል ይሆናል ። ለዚህም
ጥቂት ምሳሌዎችን በመጥቀስ እቀጥላለሁ >>>>>
(1)አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ
(2)ሩጫዬን ጨርሻለሁ
(3)ተኖረና ተሞተ ......ሌሎችም ብዙ ያልተጠቀሱ...አሉ።
እርስዎስ መቼም ክፉዎን ያርቅሎትና ሞት የማይቀር ነውና..
በርስዎ መቃብር ላይስ ምን የሚል ጥቅስ ቢቀመጥሎት ይወዳሉ ??????......

ምንጭ፡ ሙዳይ ሬድዮ
Dagem-Fikru
04/12/2011

· · Share ·

Facebook-History

FACEBOOK - HISTORY

Tuesday, March 8, 2011

I LOVE ETHIOPIA

Posted by Picasa
ፍቅርሸ ነው ድርሻዩ !!
ማቀማጠሉን ስታውቂበት
ማራራቱን ስትችይበት
ምን አቅም የተሰጠሸ
ከሌሎች የተለየሸ
አንቺ የፍቅር ተምሳሌት
የሁላችን እናት ባለቤት
ከትላንት ትላንት በስትያ
ከአጠገብሸ ሆኜ ስቧርቅ
ዛሬን ግና........
በፍቅርሸ ናፍቆት ስማቅቅ
ከባህር ማዶ አሻግሬ
አይኖችሸን ባየዋቸው
ምነው ባወሩኝ በሰማዋቸው
እማማ......
ለካንስ ናፍቆት ያንሰፈስፋል
እንደ እግር እሳት ይለበልባል
እኔስ ምን ልሁን እማማ...?
ርህራሄሸ ያሳዝነኛል
ፍቅርሸ ትንፋሸሸ
ምክር ስጦታሸ
ሁለነገርሸ ይናፍቀኛል
እማማ ዛሬም...
ትዝ አለኝ ታወሸኝ
ናፍቆት በረታ ጠናብኝ
አንቺ እኮ እናቴ ልዩ ነሸ
ከአምላክ ጸጋ የተቸረሸ
>>>>>>>>//>>>>>>>>>>

ለሁላችን እናቶች ይሁንልኝ
ዳግም ፍቅሩ
3/01/2011See More