
ተመስገን ! ጌታ ሆይ
አንተ ያረክልን
መች ከሆድ ይጠፋል
ሞትን ለኛ ሞተህ
እኛን አትርፈሃል ::
ሞትን ለኛ ሞቶ
ለሚያኖረን ጌታ ምስጋና ይገባዋል
ሁሌ ጠዋት ማታ።
አ እዋፋት ዘምረው
እንሰሳትም ጮኸው
ሰማይና ምድርም
እንዲሁ ተማክረው
ያመሰግኑሃል
ልባቸውን ከፍተው ::
ይብላኝ ለከሃዲው ለዚያ ለይሁዳ አምላኬ በስምህ
በክህደት ተጎዳ ::
አረ አንተስ ልዩ ነህ
ፍቅርህ መቼ ያልቃል
ጥሎህም የሄደው
በፍቅርህ ይወድቃል ።
ተመስገን ጌታዬ
ሁሌ ጠዋት ማታ
አንተ ያለም ንጉስ
የሁሉ አለኝታ ። ዳግም - ፍቅሩ
4/12/2011
No comments:
Post a Comment